Communities and Justice

Amharic

ለመደወል
13 21 11

እያንዳንዱ ልጃገረድ የህጻንነት ጊዜን በሚገባ በመጠቀም ለወደፊት ብሩህ ደስተኛ እድልን ማግኘት።

እድሜ ሳደርስ በግዴታ ጋብቻ።

ታዳጊ ወጣቶች ምኞታቸውን ለማሟላት አውስትራሊያ ታላቅ እድል ያቀርብላቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ማንን ማግባት እንደሚችሉ የመምረጥ መብት ይኖረዋል። እድሜ ሳይደርስ በግዴታ ማግባት የልጃገረዶችን የወደፊት ብሩህ ተስፋቸውን ማበላሸት ነው። ለትምህርት ያላቸውን ምርጫ በማቀብ በጣም ጠቃሚ የሆነን የኮረዳና የልጅነት ዓመታት ህይወት ማበላሸት ይሆናል። እንዲሁም ህገ-ወጥነት ስለሆነ ለወደፊት ብሩህ የሆነን ይምረጡ።

በግዴታ ጋብቻ ምንድ ነው?

ይህ አንድ ሰው (ወይም ሁለቱም) ያለፍላጎትና ያለሙሉ ስምምነት ጋብቻ ሲደረግ ነው። እንዲጋቡ የተደረገው በማታለል፣ በማስፈራራት ወይም በማስገደድ ሊሆን ይችላል።

አንድ ሰው ጋብቻ እንዲፈጽም እንዴት መገደድ ይችላል?

ጋብቻውን ለማካሄድ ሰዎች ነአካልና ስነ-ልቦና ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ። በዚህ ውስጥም የአካል ወይም የወሲባዊ ግንኙነት ሁከትን፣ ማስፈራራትን፣ በእስር ዘብጥያን ማካሄድን፣ ከትምህርት ቤት ማስወጣትን ወይም ጋብቻን ስላልፈጸሙ ለቤተሰቡ አሳፋሪ ወርደትን ማስከተልን ሊያካትት ይችላል።

ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ የግዴታ ጋብቻ ምንድ ነው?

ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ ጋብቻ በሌላ አጠራር በግዴታ የህጻን ጋብቻ ተብሎ ሲጠራ፤ ይህም እድሜው ከ 18 ዓመት በታች ለሆነ ሰው በግዴታ ጋብቻ መፈጸም ይሆናል።

በአውስትራሊያ ህግ መሰረት እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ለመጋባት ስምምነት ላለመስጠት ይችላሉ። እድሜያቸው 16 ወይም 17 ዓመት የሆናቸው ህጻናት መጋባት የሚችሉት ከፍርድ ቤት እና ወላጆቻቸው ፈቃድ ካገኙ ብቻ ነው። በአውስትራሊያ ውስጥ አንድ ሰው እድሜው ከ 16 ዓመት በታች ከሆነ በምንም ሁኔታ ህጋዊ ጋብቻ መፈጸም አይችልም።

ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ በግዴታ ጋብቻ ማን ያካሂዳል?

ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ በግዴታ ጋብቻ መፈጸም በማንኛውም ባህል፣ ሃይማኖት ወይም ጎሳ ነገድ የተወሰነ አይደለም።

በአውስትራሊያ ውስጥ ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ ጋብቻ መፈጸም ወንጀል ነው።

በአውስትራሊያ ውስጥ በማስገደድ ጋብቻ ህገ-ወጥነት ነሲሆን፤ ይህም እስከ ሰባት ዓመታት እስር ቤት ሊያስገባ ይችላል።

በዚህ ውስጥ ሊካተት የሚችለው ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ የሰርግ አቀናጂዎች፣ የጋብቻ ሥርዓት ፈጻሚዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ናቸው። ጋብቻው ወይም ሥርዓቱ የሚካሄደው በባህላዊ ወይም በሃይማኖታዊ ልምድ እና ጋብቻው ህጋዊ መንገድን ያልተከተለ ቢሆንም ህጉ ግን ተግባራዊ ይሆናል።

የተዘጋጀ ጋብቻ ምንድ ነው?

በግዳጅ ጋብቻ እና በቅንጅት የተዘጋጀ ጋብቻ የተለያዩ ናቸው።

በቅንጅት የተዘጋጀ ጋብቻ ማለት እድሜው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ሰው ትዳር ለማካሄድ በሆነ ሰው (ብዙጊዜ በቤተሰብ) ሲተዋወቁ ነው። ከዚያም ለመጋባትና አለመጋባት የሁለቱ ሰዎች ምርጫ ይሆናል። ሁለቱም በተቀናጀው ጋብቻ ላይ ለመስስማማት ነጻ ናቸው።

በአውስትራሊያ የተዘጋጀ ጋብቻ ቅንጅት ህጋዊነት አለው።

በህጻኑ ላይ የግዳጅ ጋብቻ ተካሂዷል በሚል ከተጠራጠሩ፤ እርዳታ ማግኘት።.

ህጻኑ ወይም ታዳጊ ወጣት እድሜው 18 ዓመት ሳይሞላ በግዳጅ ጋብቻ ስለመፈጸሙ ለማወቅ ብዙጊዜ አስቸጋሪ ነው። አንድ ሰው ለአካለ መጥን ሳይደርስ በግዳጅ ጋብቻ እንዲያካሂድ የሚል ጥርጣሬ ካለዎት ወዲያውኑ እርዳታ ማግኘት።

በግዴታ የጋብቻ ፈጻሚ ችግር ላይ ያለን እና የርስዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሁለቱንም ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። ወዲያውኑ የሚከሰት አደጋ ወይም የሁከት ፍርሃት ካለ በ 000 መደወል።

አለበለዚያ በኒውስ ሳውዝ ዌልዝ/NSW ውስጥ በቀን ለ24 ሰዓት የህጻን መከላከያ እርዳታ መስመር በስልክ 13 21 11 መደወል።

ብዙጊዜ በከፍተኛ ችግር ላይ ላሉ ህጻናት እና ታዳጊ ወጣቶች በእርዳታ መስመር በኩል በቀን ለ24 ሰዓታት ምክርና እርዳታ ሊቀርብ ይችላል። በዚህ የሚካተተው ከ18 ዓመት በታች እድሜ ላላቸው የግዴውታ ጋብቻ ችግርን ይሆናል።

እንዲሁም እርስዎ የሚያምኑት ሰው እንደ ሀኪም፣ አስተማሪ ወይም የቤተሰብ አባል ሊኖር ስለሚችል ታዲያ እድሜ ሳይደርስ በግዴታ ጋብቻ መፈጸም ስለሚቻል ጉዳይ ማነጋገር ይችላሉ።

ከእንግሊዝኛ ባሻገር ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ከሆነ ለትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት (TIS) በስልክ 13 14 50 መደወልና ወደ ህጻን መከላከያ እርዳታ መስመር (Child Protection Helpline) በስልክ 13 21 11 እንዲያገናኝዎት መጠየቅ።

ለበለጠ መረጃ

ጸረ-ባርነት አውስትራሊያ/Anti-Slavery Australia,በስልክ 02 9574 9662፣ በድረገፅ www.antislavery.org.au

የበለጠ መረጃና እርዳታ ለማግኘት በ 13 21 11 መደወል።

Last updated:

21 Apr 2023